ሊባኖስ፤ የመካነ ድር ዐውደ ርዕይ ለቅድመ ምርመራ

ሊባኖስ   ከ1940 እ.ኤ..አ ጀምሮ በሊባኖስ የተደረጉ የሳንሱር እርምጃዎችን  በመስመር ላይ የሚያስቀምጥ የመረጃ ቋት   የመካነ ድር ዐውድ ርዕይ ለሳንሱር   በመክፈት ተኩራርታለች፡፡ ይህ መካነ ድር ይፋ የተደረገው ማርች በተሰኘ የሊባኖስ ድርጅት ሲሆን ከህዝብ ርቀው ወደተቀመጡ መረጃዎች ትኩረትን ለመሳብ ነው፡፡

በመስከረም 2 ፣ 2012 እ.ኤ.አ  ይህ የመካነ ድር ዐውደ ርዕይ ለሳንሱር ይፋ ሲሆን ማርች እንዲህ ብሏል፡፡

እንኳን ወደ ሊባኖስ የመካነ ድር ዐውደ ርዕይ ለሳንሱር በደህና መጣችኹ!

በሊባኖስ ምን ሳንሱር ሲደረግ እንደነበር ፣መቼ? በተለይ ለምን? የሚለውን በማወቅ ፍጹም ለመገረም ወደ ትክክለኛው ስፍራ ነው የመጣችኹት፡፡
እዚህ ከ1940   ጀምሮ ምን አይነት ነገሮች ሳንሱር ሲደረጉ እንደነበሩ መመልከት ትችላላችኹ፡፡

ከዚህ በፊት  ሳንሱር የመደረግ አደጋ ላይ የነበሩ ወይም ከዚህ በፊት ሳንሱር ተደርገው የነበሩ እኛ ግን ለመለጠፍ ያላገኘቸው/የሳትናቸው ሳንሱር ስለተደረጉ አንዳንዶች  ነገሮች ሰምታችኃል?  ለኛ ለመጠቆም ነጻ ሁኑ ፤ ምክንያቱም የመረጃመረቡን ምሉዕ ያደርጋልና፡፡

የበየነ መረብ  ተጠቃሚዎች የሚያውቋቸው  1940  ጀምሮ ሳንሱር የተደረጉ ህትመቶችና የምስልወድምጽ ይዘት ያላቸው ፊልሞች ፣ ሙዚቃዎች ፣ ቲያትሮች ፣ መጽሐፍት  ካሉ ለመካነ ድሩ መጠቆም ይችላሉ፡፡ከእነርሱ የሚጠበቀው የታገደውን ስራ ስም ፣ የታገደበትን ቀን  ፣ምክንያት  እና የመኖሩን ምስክር መጥቀስ ነው፡፡

ለምሳሌ በ1940  የቻርሊ ቻፒሊን ግሬት ዲክታተር ጸረ ናዚ እይታ ስላለው ታግዷል፡፡ በ1990 ደግሞ ኤልቢሲ ኢንተርናሽናል  በጊዜው የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከነበሩት ዴቪድ ሌቪ ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ስርጭት እንዲያቋርጥ ከብሔራዊ የምስልወድምጽ ሚዲያ ካውንስል  ማስፈራሪያ ደርሶታል፡፡

 

በ2012 ሊባኖሳዊው ጋዜጠኛ ሙስጠፋ ገሓ ከግድያ ሙከራ ተርፏል፡፡ የሂዝቦላ መሪ ሀሰን ነርሰላን የነደፈው ካርቶኒስት ዛቻ ደርሶታል፤  የማርጄን ሳትራፒ ፐርሰፐሊስ ‘እስላምና እና ኢራንን በማስቀየም’ ከመጽሐፍ መደብር ታግዷል፡፡

በሊባኖስ ሳንሱር የሚያደርገው ማነው?  

የሳንሱር ዐውደ ርዕይ መካነ ድር  በሊባኖስ አራት ዋና የእግድ  ፈጻሚዎችን  ይዘረዝራል፡፡

ጠቅላላ ደህንነት፡ ለፈጠራ ስራዎች  ፍቃድ መስጠት፣ መቆጣጠር ፣ ሳንሱር ማድረግ

የመረጃ ሚኒስቴር : የውጭ የህመትቶች ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማዕቀብ መጣል ፣ቅጅውን በቁጥጥር ስር ማዋል ፣ በየጊዜው ለሚታተሙ የህትመት ውጤቶች እንዲታተሙ ፍቃድ መስጠት  ምን አልባትም የቴሌቪዥን ስርጭቶችን እስከ ሶስት ቀናት ሊያዘገይ ይችላል፡፡የሲኒማ ስራዎችን በቅደመ መድረክ የሳንሱር ሁደት ውስጥ በማሳለፍ ከጠቅላላ ደህንነት ጋር በመተባበር ሊያግድ ይችላል፡፡

ልዩ አስተዳደራዊ ኮሚቴ፡ ጠቅላላ ደህንነት የአንድን ፊልም በከፊል ወይም  ሙሉውን ከመታየት ለማገድ በቂ ምክንያት ካገኘ ፊልሙ እንዳለ እንዲታይ ፣ የተወሰነው ክፍል አርትኦት  እንዲሰራለት ወይንም ከናካቴው እንዲታገድ ውሳኔውን የሚያስተላልፈው  የኮሚቴው አባላት በሚሰጡት አብላጫ ድምጽ ነው፡፡የመጨረሻው ውሳኔ በመንግስት ደረጃ የሚሰራጨውው በሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡

ብሔራዊ የምስልወድምጽ ሚዲያ ካውንሰል፡ ካውንስሉ ‘የሚዲያው ጠባቂ ውሻ’ ሆኗል፡፡ ስራውን የጀመረው መንግስት የራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለመቆጣጠር  የሚያስችል አማካሪ ቦርድ ሆኖ ነው፡፡አሁን  የካውንስሉ ባለስልጣን መካነ ድሮች እና ጦማሮችን ለመጨመር  በመስፋፋት ላይ ነው፡፡ (ምን?  ድኀረ ሳንሱርን በቴሌቪዥን በራዲዮና በበየነ መረብ ላይ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

የሳንሱር መግፍኤዎች

በሊባኖስ የሳንሱር ልምዶች  ፖለቲካዊ ፣ ሀይማኖታዊ ወይም የሞራላዊ መግፍኤዎች  ውጤት ናቸው፡፡የሳንሱር ዐውደ ርዕይ መካነ ድር እንዲህ ሲል ያብራራል፡፡

ፖለቲካዊ ምክንያቶች፡  ከወዳጅ ሀገራት ጋር የሚደረግ የውጭ ግንኙነትን በተመለከተ የሳንሱር ሂደቱ  ለአረብ  ሀገራት የአገዛዝ ስርዓቶች ፖለቲካዊ ትኩሳቶች ላቅ ያለ ትኩረትን ይሰጣል፤ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያለን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ለመጠበቅ ጥረት ያደርጋል፡፡ ጎን ለጎንም በፍልስጤም ጉዳይ በአጠቃላይ አረቦች ላይ ጥቃት የሚያደርሱት ላይ  እግድ ይጥላል፡፡ከዘጠናዎቹ ጀምሮ “የሲቪል ሰላም በማስፈራራት” እንደመሰረት በመጥቀስ በእርስ በርስ ጦርነትን የሚያሳዩ   ፊልሞችበተደጋጋሚ ታግደዋል፡፡

እስራኤል፡ ከጠላት ሀገር ጋር ያለ ግንኙነትን በተመለከተ መጀመሪያ ሳንሱር መሰረት ያደረገው የእስራኤል ምርቶችን በሙሉ አለመጠቀምን የሚጠራውን ብሔራዊ ህግ ነው፡፡ በመቀጠል ለእስራኤል ሁሉም አይነት ቅርጽ ያላቸው ማስተዋወቆች ወይም  ርህራሄ  ያላቸው ነገሮች ለእግድ ተዳርገዋል፡፡ይህ እስራኤል ላይ የተጣለ እግድ በመነሻ በመላው የአረብ ሊግ ሀገራት  ነበር፡፡ዛሬ  ሊባኖስ እና ሶርያ ብቻ በትጋት እንዲፈጸም ይጥራሉ ፡፡(…)

ሀይማኖት፡ ጠቅላይ ደህንነት የፈጠራ ውጤቶች  ሀይማኖታዊ ቁጣዎችን የሚቀሰቅሱ ናቸው ብሎ ካሰበ  ወደሚመለከታቸው አካላት (አብዛኛውን ጊዜ ለካቶሊክ የመረጃ ማዕከል ወይም በሊባኖስ ትልቁ የሱኒ ሙስሊም ባለስልጣን ለሆነው ለዳር አል ፈጣዋ ) ይልካቸዋል፡፡  ገቢሮች ወይም ርዕሶች የሀይማኖትን አቅም ምላሽ  የመጠየቅ ለመጻረር አቅም ካለውና የሚያስቀይም ከሆነ ገቢሮቹ ይወገዳሉ፡፡

የብልግና እና ኢሞራላዊ  ይዘቶች፡ የህብረተሰቡን ሞራል የሚነካ ውጤትን በተመለከተ  ሳንሱር የሚደረገው ራቁት ገቢር ፣ ወሲብና ጋጣወጥ ቋንቋን ያካተተ ከሆነ የግድ ሳንሱር ይደረጋሉ የሳንሱር  ምርመራው የሚጠበቅበት ፊልምም ሆነ ሌላ ስራ የህብረተሰቡን ሞራል የማይነካ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታቱ ስራዎችም የተከለከሉ ናቸው፡፡  የአመጽ ገቢር ወይም የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት የሚወክሉ ገቢሮች ግን የተፈቀዱ ናቸው፡፡

የቲዊተር ምላሾች

በትዊተር ይህ ስራ መልካም ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡

@SultanAlQassemi፡ ይህ በጣም ጠሩ ዐሳብ ነው ፡፡ የሳንሱር ዐውደ ርዕይ መካነ ድር (ሊባኖስ)censorshiplebanon.org via @Sandmonkey ሁሉም የገልፍ ሀገሮች አንዳንድ ያስፈልጋቸዋል፡፡

@mirabaz: ይህ ታላቅ ነው፡፡ምንድን ነው ሳንሱር የተደረገው መቼ እና ለምን– -> censorshiplebanon.org v @SultanAlQassemi

@ramseygeorge: ይህ ድንቅ ነው

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.