በኬኒያ ቴሌቭዥን የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የሃይማኖት ተቋማትን አስቆጣ

በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ይውል ዘንድ HIV እና ተዛማጅ በሽታዎችን ለመከላከል የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ማስቆጣቱን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ታገዷል፡፡

ማስታቂያው አንዲት ባለትዳር ሴት ባለቤቷ ከትዳር ውጪ በሚያደርጋቸው የግብረስጋ ግንኙነቶች ኮንዶም እንዲጠቀም ምክር ስትሰጠው የሚያሳይ ሲሆን ማስታወቂያው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዩኤስ ኤድ እና ዩኬ ኤድ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተዘጋጀ ነው፡፡

የኬኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፒተር ቼሩቲች ለBBC ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ማስታወቂያው የተሠራው ከባለ ትዳሮች መካከል 30 በመቶዎቹ ከትዳር ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ግንኙነቶች ስላላቸው ነው ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት ከሆነ ደግሞ ኬኒያ ካላት 41.6 ሚሌኒየን ሕዝብ መካከል 1.6 ሚሊየን ሕዝቦች HIV በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡

የክርስቲያን እና የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች ግን ማስታወቂያው ከትዳር ውጪ መወስለትን ያበረታታል ሲሉ አውግዘውታል፡፡

የኮንዶም ማስታወቂያው  ከኬኒያ  ቴሌቨዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች ላይ መተላለፉ ቢቀርም በዩቲዩብ ግን አሁንም መመልከት ይቻላል፡-

The Squared Factor የተሰኘው ጦማሪ ማስታወቂያው ከቴሌቭዥን  ዕይታ ስርጭት መታገዱን ተከትሎ የሕዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ እገዳውን ተዋውሟል፡፡ “Sikio la kufa halisikii Condom” በሚል ርዕስ ባቀረበው ጽሑፍ በጥሬ ትርጉሙ የሚሞት ጆሮ  ለኮንዶም ምላሽ የለውም የሚል ሲሆን ተመሳሳይ ተርጉሙም “የሚሞት ጆሮ መዳኃኒት ቢሰጠውም መሞቱ አይቀርም ” በማለት ማስታወቂያው እንዲመለስ ጠይቋል፡፡

ዙሪያ ጥምጥም አልሽከረከርም፡፡ በጋብቻ ላይ ተደምሮ ለሚኖር ግብረስጋ ግንኙነት ኮንዶም ተጠቀሙ የሚለውን ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙኃን እንዳይታይ ለሚመክሩ ሰዎች ግምባሬ የተቋጠረ ነው፡፡

የኮንዶም ማስታወቂያው ዋንኛ መልዕክት የኅብረተሰቡን የልብ ትርታ የነካ ነው፡፡ መታቀብ አሊያም በአንድ መወሰን ካልተቻለ ለሚወዱት ሲሉ ኮንዶም በአግባቡ መጠቀም ነው፡፡ “ለሚወዱት ሲሉ” የሚለው አባባል በዚህ አገባቡ ካልተፈለገ እርግዝና ከአባላዘር በሽታና  እንዲሁም HIV እና HIVን ተከትለው ከሚመጡ ማኅበራዊ ችግሮች ቤተሰብን እና አጠቃላይ ማኅበረሰብን ማዳን የሚለውን ሐሳብ ይይዛል፡፡

ይህንን የቴሌቭዥን የኮንዶም ማስታወቂያ በተመለከተ #CondomMpangoni የሚል ሃሽ ታግ በመፍጠር ኬኒያውያን ማስታወቂያውን በመደገፍ እና በመቃወም ውይይታቸውን ወደ ቲውተር ይዘው መጥተዋል፡፡

“ቪክቶር-MUFC” (‏@victorbmc) ማስታወቂያውን እንደዳልወደደው ጽፏል፡-

“ቪክቶር-MUFC” (‏@victorbmc) ያ ማስታወቂያ የማይረባ ነው፡፡ RT @MacOtani: ዋው አሁን የ#CondomMpangoni (ኮንዶም) ማስታወቂያው ከቴሌቭዥናችን ስክሪን ስለጠፋ እኛ ደህና ነን ማለት ነው፤ አዪ?! #SwalaNyeti

ማቲያስ ናዴታ (‏@MNdeta) ደግሞ ማስታወቂያውን የተቃወሙ ኬኒያዎች እውነታውን እንደዲጋፈጡ ይናገራል፡-

(@MNdeta) በኔ አስተሳሰብ የኮንዶም ማስታወቂያው  #CondomMpangoni በቴሌቭዥን መተላለፉ መቀጠል አለበት፡፡ የሚቃወሙት አስመሳዮች ናቸው፡፡ እውነታውን እንጋፈጥ፡፡

“ዘ ጎስት ቡስተር” (‏@TheMumBi) ደግሞ አስጠንቋል፡-

(‏@TheMumBi) አንገታችንን አሽዋ ውስጥ በጣም እንቀብራለን፡፡ ስለተሠራው የኮንዶም ማስታወቂያ #CondomMpangoni አሜን ይሁን፡፡ ማስታወቂያው በመሠራቱ ለማውራት እንሸሸው ስለነበረ ጉዳይ እንድናወራ አስገድዶናል፡፡

ፖል (‏@M45Paul) የማስታወቂያው መታገድ ይበልጥ እንዲተዋወቅ አድርጓል ሲል ይሞግታል፡-

(@M45Paul)  የኮንዶም ማስታወቂያውን #CondomMpangoni ማገድ በራሱ ማስታወቂያው በተለመደው የቴሌቭዥን ስርጭት ያገኝ ከነበረው ዕይታ ተጨማሪ ተመልካች እንዲያገኝ ረድቶታ፡፡

“ፓስተር ዋ ” (‏@Pastor_Wa) ምክር ሰጥተዋል፡-

(‏@Pastor_Wa) ማንኛውም ማስታወቂያውን የተመለከተ ሰው በልቡ “እኔ ከዚህ ማስታወቂያ እሻላለሁ” እንዲል ተገዷል፡፡ #CondomMpangoni

“ኬዚ ኬ*” (‏@boobykizzy) ጠይቋል:-

‏@boobykizzy: ክብር፣ ሞራል፣ ስብዕና የሚባል ነገር የለም? መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያውን #condommpangoni በማስነገራቸው መወቀስ አለባቸው? ወይስ ለችግሩ እልባት መስጠት አለብን?

በመጨረሻ አቬሬጅ ኬኒያ (‏@AverageKenyan) ያሰቀመጠው፡-

‏@AverageKenyan: #Condommpangoni,እውነታውን አለመቀበል አይደለም፡፡ ውስብስብ የሆነው የአፍሪካ የባሕል ስብጥር ምንም እንኳን ነገሩ እውነት ቢሆንም በትዳር ላይ መወስለትን በተመለከተ በአደባባይ ድጋፍ አይሰጥም፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.