“V for Vendetta” የተሰኘው ፊልም ሳንሱር አለመደረግ ቻይናውያንን አስደመመ

V for Vendetta የተሰኘው እና እ.ኤ.አ. በ2005 የተሠራው፣ ስለተበደሉ ማኅበረሰቦች የሚያወራ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ቀድሞ በቻይና እንዳይ ታግዶ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ባለፈው አርብ ታኅሳስ 5/2005 በቻይና የማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (CCTV) ስድስተኛው ጣቢያ ታይቷል፡፡ በተለይም የመንግሥታትን ጭቆና ለመቃወም በመላው ዓለም ጭቆናን የመቋቋም ትዕምርት ሆኖ በአራማጆች የተመረጠው ‘V’ ሳይቆረጥ/ሳይወጣ መታየቱ በርካቶችን አስደምሟል፡፡.

ፖለቲካዊ ክስ ያለበትን ፊልም ማጫወት

loveforchina በተባለ ተጠቃሚ የተሰቀለው የሚከተለው የዩትዩብ ቪዲዮ የሚያሳየው አራማጆች ፊልሙን ተጠቅመው በቻይና ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት ለመቃወም እንዴት እንደተጠቀሙበት ነው፡-

 

ለዚያ ነው የCCTV ተግባር ሲና ዌይቦ በተሰኜ የጥቃቅን ቻይናዊ ጦማሮች መደበአለፍ ላይ የሞቀ መወያያ ለመሆን የበቃው፡፡ ጉዳዩ ሁዋቲ [zh], (ርዕሰ ውይይት) መደበአለፉ ላይ ተበጅቶለት በአጭር ግዜ ውስጥ 3,469 ምልልሶችን አስተናግዷል፡፡

የትራምፔት ጥቃቅን ዜናዎች (喇叭微新聞 ይህንን የሞቀ ውይይት ርዕሰ ዜና [zh] አድርጎት ነበር፡-

 

‘V’ የቻይናን ማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ተቆጣጠረው፡፡ የትዊተር ተጠቃሚው ኩንሹ በፎቶሾፕ ያዘጋጀው ምስል

NOW!CCTV6正在播出《v字别动队》(又名《V字仇杀队》)。应该算是大陆首播了!

አሁን! CCTV6 ‘V for Vendetta’ን እያሳየ ነው፡፡ ይህ በቻይና ሜይንላንድ ሲታይ የመጀመሪያው መሆን አለበት፡፡

ዜናው ብዙዎችን ወደውይይቱ እንዲቀላቀሉ አደረጋቸው፡-ዜናው ብዙዎችን ወደውይይቱ እንዲቀላቀሉ አደረጋቸው፡-

橐橐:禁播才心里有鬼,放开后发现其实也没什么大不了,也许中国不要中共的领导也不会有什么啦,一切都是猜测。

橐橐:ቅድመ ምርመራ ማለት በ[ባለሥልጣናቱ] ልብ ውስጥ የሙት መንፈስ አለ ማለት ነው፡፡ ቅድመ ምርመራው አንዴ ከተነሳ፣ ሁሉም ነገር ወደመደበኛነት ይመጣል፡፡ ምናልባት ቻይና የኮሙኒስቱን ፓርቲ አመራር አትፈልግ ይሆናል፤ እርግጥም ይሄ አመላካች ነው፡፡

叶孤城蝶恋花:知道CCTV6播V确实是激动了半天,感觉天朝还是有希望的,就是没想通怎么要改成个别动队,求解释

叶孤城蝶恋花:: CCTV 6 ይሄንን ‘V’ በማሳየቱ ተደስቻለሁ እናምተስፋ እንዳላት ተሰምቶኛል፡፡ ቢሆንም ግን የፊልሙን ርዕስ (ከ“V የበቀል ግድያ አንጃ” V字仇殺隊)ወደ “V አትንቀሳቀስ ቡድን” (V字別動隊 – ወይም V የኮማንዶ ቡድን) እንደቀየሩት አልገባኝም፡፡ የሚያብራራልኝ ይኖር ይሆን?

ቅድመ ምርመራ ወደፊት ይቀንስ ይሆን?

ቻይና ዲጂታ ታይምስ እንደተጠቆመው ከፊልሙ ርዕስ በቀር ይዘቱ ምንም አርትኦት አልተካሄደበትም፡፡ የሎስ አንጀለሱ ኤንጅል እንደጠቆመው [zh] የአገሪቱ ሬዲዮ ፊልምና ቴሌቪዥን አስተዳደር(SARF)  ለCCTV 6 ፕሮግራም ሙሉ ኃላፊነት አለበት፤ ለዚያ ነው ይህ ጉዳይ ፖለቲካዊ አንድምታ የሚኖረው፡-

2月14日晚,大陆央视电影频道首次播放了禁片《V字别动队》,该举动引发了了网友们的热议,很多人甚至在怀疑自己的眼睛或者是电影频道的编审们睡过了头。不过,据圈内人介绍,央视电影频道名义上属央视,但该频道播出与制作分离,行政上由国家广电总局负责,

በታኅሳስ 5 ምሽት፣ CCTV…'V for Vendetta’ የተሰኘውን ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ አስተላለፈ፡፡ እርምጃው የድር-ዜጎችን በጣም አወያይቷል፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም የቻናሉ ቴክኒሻኖች እንቅልፍ ወስዷቸው ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ከቲቪው ዙሪያ እንደምናውቀው የዝግጅቱ እና ስርጭቱ ሁኔታ በCCTV ውስጥ ለየብቻው ነው፡፡ የአስተዳደሩን ሙሉ ኃላፊነት የሚወስደው SARF ነው፡፡

ግሎባል ታይምስ (የመንግሥት ይዞታ የሆነ መገናኛ ብዙኃን ሳይቀር) የድር-ዜጎችን ምላሽ በመቀነጫጨብ በጥቃቅን ጦማሮቹ ላይ አስተናግዶ ጥቂት ትችቶችን ተቀብሏል፡-

南扉:能不能放,不是由老百姓说了算。制度不改革,老百姓只能旁观是明君还是昏君

南扉:ፊልሙ ሊታይ ይችላል ወይም አይችልም የሚለው የሚወሰነው በሕዝቡ አይደለም፡፡ በሥርዓቱ ውስጥ ተሐድሶ ካልተካሄደ በቀር ሕዝቦች አስተያየታቸውን መስጠት የሚችሉት ንጉሡ ጥሩ ነው መጥፎ በሚለው ላይ ብቻ ይሆናል፡፡

我愛壹玖捌柒:该上船的早已经上去了,谁还管你电视放什么电影,既然这样,把那部三个小时的《天安门》也放一下吧。

我愛壹玖捌柒:ለመሄድ የወሱነት እንደሁ አንዴ ሄደዋል፤ ምን ዓይነት ፊልም ታየ የሚለው ማንን ይገርመዋል፡፡ ከፈለጉ ለምን የሦስት ሰዓቱን ፊልም አያሳዩም – ታይናንሜንን?

Cupid_Yes:干脆把局域网也开放点?

Cupid_Yes:ለምን Great Fire Wall (የቻይና የበይነመረብ ይዘት ማጥለያን) አትከፍቱልንም?

静静的粉玫瑰:真心希望这是一个好的信号。其实中国一直是一个有深厚文化底蕴的国度,非常怀念春秋战国时期百家争鸣,各种思想家争相涌现的时代。解放思想,文化多元,这个国家才有希望,才会让脚踏实地地人们学会仰望星空。

静静的粉玫瑰:ጥሩ ምልክት ነው ብዬ ተስፋ አድርጌያለሁ፡፡ ቻይና የብዙ ባሕል አገር ናት፡፡ ፀደይ እና በልግ እየተዋጉ ብዙ የዐሳብ ዐውዶች እርስ በእርሳቸው የሚፎካከሩባት አገር እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ አገር ተስፋ የሚኖራት አስተሳሰቦችን እና ብዝኃ ባሕሎችን ነጻ ስታወጣ ነው፡፡ እስከዚያው ግን ሕዝቦች ደረቅ መሬት ላይ ተቀምጠው ኮከባማ ሰማይ ላይ ያማትራሉ፡፡

አሻጋሪ ጦማሪዎች (Bridge bloggers) ዜናውን ወዲያው ነው ያስተጋቡት፡፡ ብሬንደን ኮኔሊ ፊልሙ መታየቱን አስገራሚ ሆኖ አግኝቶታል:-

ስንት ሚሊዮኖች ይህንን በተበላሸ አገዛዝ ላይ ጭምብል ለበስ አብዮት የሚመራ ታሪክ እንዳዩ ምንም አላውቅም፤ መገመት የምንችለው ምን ዓይነት ባሕላዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር – ወይም እንደማያሳድር – ብቻ ነው፡፡ በጣም በቅርቡ፣ ምናልባት ሁሉም ርካሽ V ቅርጽ ያላቸው ጭምብሎች በቻይና ብቻ ላይሠሩ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ በቻይና የስርጭት ባሕል ተቀየረ ማለት ነው? ዢ ጂንፒንግ ኅዳር 6 የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲን ዋና ጸሐፊ ቦታ ይዟል፤ ምናልባት በውስጡ የተሻለ ተራማጅነት ባሕርይ አዳብሮ ይሆናል…

ምናልባት ‘V’ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ጊዜ ነው የሚነግረን፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.