የትርጉም መርሐ ግብር፤ ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነትን ጥበቃ መግለጫ

ለተከታዮቹ ሰባት ቀናት የዓለም ድምፆች የቋንቋ በጎ ፈቃደኞች፤   ህዝባዊ የመስመር ላይ የድጋፍ ፊርማን ይተረጉማሉ፡፡ ፊርማው በመጪው ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይቲዩ) ጉባኤ ላይ የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት ጥበቃን የሚደግፍና የአይቲዩ አባላት የሆኑ መንግስታትን የበየነ መረብ ገሀድነት እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ነው፡፡

ለማንኛውም ግለሰብ ወይም የሲቪል ማኀበር ፊርማ ክፍት የሆነው አለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ጥበቃ መግለጫ እንዲህ ይነበባል፤

በታህሳስ 3(እ.ኤ.አ.)  የዓለም መንግስታት ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ህብረት (አይ.ቲ.ዩ) የተሠኘውን የመንግስታቱ ህብረት ኤጀንሲ ቁልፍ ስምምነት ለማደስ ይገናኛሉ፡፡ አንዳንድ መንግስታት የበየነመረብ ገሐድነትና እና ፈጠራዎችን በሚገድብ፣  የመገልገያ ወጪን በሚጨምር፣ የመስመር ላይ ነጻነትን በሚሸረሽር መልኩ የአይቲዩ ስልጣን የበየነመረብ ገዢነት በመጨመር እንዲሰፋ ሐሳብ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡የሲቪል ማኀበራት ድርጅቶችና የሁሉም ሀገራት ዜጎች ዓለምአቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ለመጠበቅ ይህንን መግለጫ እንዲፈርሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የበየነ መረብ አስተዳደር ውሳኔዎች መደረግ ያለባቸው  በግልጽነት በትክክለኛ ብዙኃን ባለድርሻ አካላት፣ በሲቪል ማኀበራት፣ መንግስታት እና የግሉ ማኀበረሰብ  ተሳትፎ ነው፡፡  አይቲዩን እና አባል ሀገራቱን ግልጸኝነት እንዲመርጡና ምናልባት  የመስመር ላይ ሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴን የሚጎዳውን የአይቲዩ ስልጣን ወደ በየነ መረብ ገዢነት የመስፋፋት  ምንም አይነት ሐሳብ ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የተቃውሞውን ፊርማ ለማኖር ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ነጻነት ጥበቃን መካነ ድር ይጎብኙ፡፡ ለመፈረም የመጀመሪያ ስሞዎን፣ የቤተሰብ ስሞዎን፣  የበየነ መረብ አድራሻዎትን፣ የደርጅትዎን ስም (የሲቨል ማኀበራት ድርጅትን ወክለው የሚፈርሙ ከሆነ)፣ የደርጅትዎን መካነ ድር ያስገቡ፤ ሀገርዎን ከዝርዝሩ ውስጥ ይምረጡ፡፡

ሁሉም ትርጉሞች በተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰቢያው መካነ ድር መቀመጫውን ካናዳ ባደረገው የዲጂታል መብቶች ቡድን ኦፕንሚዲያ ወደመስመር ላይ በሚሰቅለው ላይ ይለጠፋሉ፡፡

እባክዎን ትርጉሙ በሚታይበት ጊዜ(ከላይ ያለውን ይመልከቱ) በማኀበራዊ ሚዲያዎች ለወዳጆቻችኹ ለማጋራት የበረታችኹ ሁኑ፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.