ታሪኮች ስለ አረብኛ
ቪዲዮ፤ “ኖ ዉማን፣ ኖ ድራይቭ” ሳኡዲ አረቢያን አደመቃት
ዛሬ፣ ጥቅምት 16፣ 2006 ለሳኡዲ አራማጆች በኪንግደሙ ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የተጣለባቸው ማዕቀብ ላይ ለማመጽ የመረጡት ቀን ነበር። የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች በአገሪቷ ውስጥ መኪና እየነዱ ስለታዩት ሴቶች ቁጥር መጨመር በስፋት እያወሩ ሳሉ፣ ተወዳጁ፣ የቦብ ማርሌይ “ኖ ዉማን፣ ኖ ክራይ” የተሰኘ ዜማ ሴቶችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን ለመንፈግ የወጣ የወግ አጥባቂ ስርዓተ ፆታ...
በኪዌት ህቡዕ የትዊተር ገጽ ታላቅ ተቃውሞን እየመራ ነው
ባለፉት ጥቂት አመታት አመጸኞቹ በተቃዋሚ የፓርላማ አባላት በመመራታቸው ትችት ደርሶባቸዋል፤ በኋላ ወጣቶቹ የተቃውሞው መሪዎች ለመሆን ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ "የክብር ሰልፎች" ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡ሌላው አስገራሚ የሚያደርገው ነገር ደግሞ የሁለቱም ሰልፎች ቀንና መነሻ ቦታ የተወሰነው በህቡዕ የትዊተር ገጽ መሆኑ ነው፡፡
ባህሬን፤ ዴሞክራሲና እስልምና አንድ ላይ መኖር ይችላሉ?
‘በኢስላማዊ ማኀበረሰብ ዴሞክራሲ ሊኖር ይችላል? ’ዛሬ ይህ ርዕስ በባህሬናውያን ጦማሪዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኗል፡፡