ጥቅምት, 2012

ታሪኮች ከ ጥቅምት, 2012

ኢትዮጵያ አሸነፈች፤ ልጆቿም የእርግብ አሞራ እያሉ ፈነጠዙ

  14 ጥቅምት 2012

የወያኔ ካድሬዎችን ያህል በሕዝብ ደስታ የሚበሳጭ አንድ ፈልጎ ማግኘት ይቸግራል። ምነው ሸዋ፣ ዛሬኳ ቢተውን ምነው?! አሁን ማን ይሙት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኳሱ ምን አበርክተው ነው ይሄ ሁሉ የታሪክ ሽሚያ? ማስታወሻነቱማ የሚገባው ብርድና ሃሩር ሳይል ለኣመታት መከራውን የበላው ሕዝብ ነው።

ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያን የቡድናቸውን ማሸነፍ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው

  14 ጥቅምት 2012

ምንም እንኳን የእግርኳስ ውጤት በአብዛኛው በጨዋታዎች እለት በሚፈጠሩ ክስተቶች ላይ ጥገኛ ቢሆንም ታሪክ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያደላል። የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች በአንዱም ያላሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ሁለቱ ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጓቸው ሶስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ሶስቱንም ጨዋታዎች አሸንፋ ሰባት ጎሎችን ተጋጣሚዋ ሱዳን ላይ ስታስቆጥር፤ የተቆጠረባት አንድ ጎል ብቻ ነው።

ኬንያ፤ ራሳቸውን ገንዘብ-ይገዛናል ብለው ያሉ ቡድኖች ‘የካምፓስ ቀውጢ-ቺኮችን ለሀብታሞች’ አቀረቡ

  12 ጥቅምት 2012

የካምፓስ ቀውጢ-ችኮች ለሀብታሞች (Campus Divas For Rich Men) ከ26 ዓመት በታች የሆኑ የኬንያ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን በማንኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሀብታሞች ‘ለማጣበስ’ የተፈጠረ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ገጹ የተጠቀመበት መሪ ቃል “ገንዘብ-ይገዛናል” የሚል ነው፡፡

የጦማር የተግባር ቀን 2012፡ ‘የእኛ ኃይል’ በሚል መሪ ርዕስ ይከበራል

እንግዲህ ከ95 ሀገሮች የተውጣጡ ጦማሪያን በነዛ ብቁ እና ፈጣን እጆቻቸው ሊከትቡ ተዘጋጅተዋል፡፡ ለአንድ ቀን ሁሉም ስለ አንድ ተመሳሳይ ጉናይ ላይ በመፃፍና የሚያምር የታሪክ ፍሰት በመስራት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተካታዮቻቸው ይጦምራሉ፡፡ ጥቅምት 15፣ 2012 – የጦማር የተግባር ቀን ! ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የጦማር የተግባር ቀን በጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ንቃትን ለመፍጠር፤ የጦማር ጥቃት...

በቻይና ፡ አንድ ተማሪ የንግግር ነፃነትን ለመከላከል ጫማውን ወረወረ

አንድ የሃይናን ዩንቨርስቲ ተማሪ በኦክቶበር 7፣ 2012 ዓ.ም በቻይና የመናገር ነፃነት አለመኖርን ተቃውሞ ሲማ ናን በተባሉ ማኦይስት ሀያሲ ላይ ጫማውን ወረወረ፡፡ ጫማውንም ከመወርወሩ በፊት ‹‹ምንም እንኳን የምትናገረው ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ወደ ሆቴልዎት መመለስ ይችላሉ፤ ነገር ግን እኔ ንግግሩን ብቃወም ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደሚዘጋብኝ እርግጠኛ ነኝ ፡፡›› ብሏል፡፡ ተማሪው ርምጃውን...

በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ

  10 ጥቅምት 2012

በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣ ብጉር ማውጣት ፀጉር ማብቀል፣ የደም ግፊት እና እንደ የሰኳር በሽታ አይነት ጉዳቶች በተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ናቸው፡፡ በሴኔጋል ቆዳን የሚያቀላው...

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ

  1 ጥቅምት 2012

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን  ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ  መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ ብቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፐሬሽን፣ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ  ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች መካነ ድሮች ተመዝብረዋል፡፡   ይህን ተከትሎ...