27 መስከረም 2012

ታሪኮች ከ 27 መስከረም 2012

ኢራን ጎግል እና ጂሜል እንዳይታዩ አገደች

እገዳው የተላለፈበተት ምክንያት ህዝቡ ብዙዎች እንደ ስድብ ቃል የሚያዩት በዩቱዩብ የሚገኘውን ጸረ እስላም ፊልም እንዲቃወሙ ነው (ዩቲዩብ የጎግል ንብረት ነው)፡፡ ኮራማባዲ “የወንጀል ይዘት ያላቸው ቅጽበቶች ድንጋጌ ኮሚሽን” ቁልፍ አባል ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንዳንዶች የጎግል መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከመስከረም 22 ጀምሮ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን እስካሁን ግን ብቅ ያላለውን የኢራናውያን ብሔራዊ በየነ መረብ የበለጠ ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ኡጋንዳ፤ ከአሥራዎቹ ዕድሜ ያልተሻገረች ሴት የአፍሪካ ትንሽዋ የፓርላማ አባል ሆነች

  27 መስከረም 2012

አፍሪካ እና የአፍሪካ ሴቶች የምር እያደጉ ነው:: የማላዊ እና የላይቤሪያ ፕሬዚደንቶች ሴቶች ናቸው:: አሁን ደግሞ ኡጋንዳ በዕድሜ ትንሽዋን የ19 ዓመትዋን ሴት የፓርላማ አባል ፕሮስኮቭያ አሌንጎት ኦሮሚያት መርጣለች::