የNSA ስለላን በተመለከተ ካርቱኖች ይላኩና፣ 1000 ዶላር ይሸለሙ

Commander Keith Alexander on bridge

“ኮማንድር ኬት አሌክሳንደር ድልድዩ ላይ” ካርቱን በዶንኪይ ሆቴይ (CC BY-SA 2.0)

ዘ ዌብ ዊ ወንት ካርቱኒስቶችን፣ የዲዛይን ፈጣሪዎችን እና አርቲስቶችን መልሰን የምንታገልበት ቀን በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 11፣ 2014 የበይነመረብ ስለላን እና የግለሰብ ደኅንነት መብትን በተመለከተ ወጥ የካርቱኖች ውድድር ውስጥ እንዲሳተፉ እየጋበዘ ነው፡፡ ካርቱኖቹ በNSA (የአሜሪካው ብሔራዊ ደኅንነት ኤጀንሴ) ዙሪያ መረጃ ማስጨበጥ የሚችሉ እና በጥቅሉ ለሚደረጉ የበይነመረብ ስለላዎች ተጠያቂነትን የሚፈልጉ ሆነው ሰዎች ክሊክ አድርገው ለወዳጆቻቸው ሊያጋሯቸው የሚፈልጉት ዓይነት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ካርቱኖቹን የማስረከቢያ ቀን ከ የካቲት 1 በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡

ሽልማቶች:-

1ኛ ተሸላሚ:- 1000 የአሜሪካን ዶላር
2ኛ ተሸላሚ:- 500 የአሜሪካን ዶላር
3ኛ ተሸላሚ:- 250 የአሜሪካን ዶላር

መመሪያዎች፡-

1. ሁሉም ሰው መሳተፍ ይችላል፤
2. ሥራዎቹን የሚልክ ሰው Creative Commons 4.0 ሥራዎቹን እንዲያጋሩት ተስማምቷል ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው የሚልከው ሥራ ብዛት ገደብ የለውም፤
3. ተወዳዳሪዎች ለሚልኩልን ሥራዎቻቸው ስም (ወይም የውሸት መለያ ስም) ይሰጣሉ፤ አሸናፊዎች ተጨማሪ የግል መረጃዎችን እንዲሰጡ ይጠየቃሉ፡፡ ነገር ግን ደራሲዎቹ እውነተኛ ስማቸው እንዲጠበቅ ከጠየቁ ይፋ አይደረግም፤
4. አሸናፊዎቹ የካቲት 4፣ 2006 ይገለጻሉ፡፡ አሸናፊዎቹ የሚመረጡት በ‹ዌብ ዊ ወንት› የበላይ ኮሚቴ አባላት ነው፤
5. ሽልማቱ ለአሸናፊዎቹ ውጤቱ በታወቀ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲተላለፉ ይደረጋል፡፡

ውድድሩን ለመላክ:-

1. ኢሜይል:- ከፍተኛ ጥራት ያለውና በሚከተሉት የፋይል ዓይነቶች የተዘጋጁትን ካርቱኖች፣ ማትም በ.jpg፣ በ.pdf፣ በ.svg ወይም በ.png የተዘጋጁትን መወዳደሪያ ስዕሎች በኢሜይል አድራሻ grants@webfoundation.org ርዕሱ:- Cartoon by February 8th ተብሎ ይላክ፤
2. ትዊተር፡- ሥራዎቹን በትዊተር ለመላክ @webwewant ታግ በማድረግና #webwewant ሀሽታግ አብሮ በማኖር ትዊት ማድረግ ይቻላል፤
3. የተወዳዳሪዎች ዜግነት እና አገር አለመላክ ይቻላል ነገር ግን ቢላክ ይበረታታል፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.