ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር

ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር  ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት  ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲ የሆነው ‹የብሔራዊ ድኅነት ኅብረት› (Union for National Salvation) ቃል አቀባይ ዳሃር አሕመድ ፋራህ የምርጫው ውጤት ከተነገረ በኋላ አመፅ አነሳስተዋል በሚል ምክንያት ለሁለት ወራት ያክል በተመሳሳይ ዝግ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ተፈርዶባቸው ነበር[fr] ፡፡ ቀጣዩ ቪዲዮ በፖሊስ እና በተቃዋሚ ሰልፈኞች መካመል የተነሳ ብጥብጥ ያሳያል፡፡  (via Dillipress):-

ምርጫ እስካሁንም ድረስ በጅቡቲ እውነተኛ የፖለቲካ አማራጭ ወደ ስልጣን የሚመጡበት አልሆነም፡፡ እስማኤል ኡመር ጉሌህ  እ.ኤ.አ ከሚያዚያ 9 ቀን 1999 ጀምሮ ስልጣን ላይ የተቀመጠ ሲሆን ሃገሪቷ ነጻነቷን ከተቀናጀች ጀምሮ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ የሆነው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› ስልጣኑን ይዟል፡፡

የቲንክ አፍሪካ ፕሬስ ጸሐፊው ጀምስ ሽናይደር ሁሌም የምርጫው መኖር የዴሞክራሲ ማስመሰያ እንደሆነ ያምናል፡-

የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ጊዜ ዳግም ምርጫ እ.ኤ.አ. በ2011፣ ሕገ መንግሥቱ ለሦስተኛ ጊዜ አንድ ፕሬዝዳንት ዳግም እንዲመረጥ ፈቅዶ ከተቀየረ በኋላ የተደረገ ነው፡፡  ምርጫው የምርጫ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተደረገ እናም ጉሌህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንግልት ደርሶብናል፣ ኢ-ፍትኃዊ ተግባራት ተፈፅመውብናል ብለው አቋርጠው በወጡበት ሁኔታ አሸነፈ፡፡ [..] የጉሌህ ማታለል ለአጭር ጊዜም ቢሆንም ተሳክቷል፡፡ አሁንም ስልጣን ይይዛል፣ ያለምንም የፓርላማ አባል ተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ፡፡ እርግጥ ነው በርካታ ሰዎች ከምርጫው ማታለል ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተጠቃሚዎች ተራውን የጅቡቲ ሕዝብ የሚያካትቱ አይደሉም፡፡ የሆነው ሆኖ ነጻነትን ፣ ልማትን እና የዜጎች ደኅንነትን በማታለል ብቻ ሆኖ ማሻሻል አይቻልም፡፡

Djibouti European Quarter via Wikimedia - Public Domain

በጅቡቲ የአውሮጳውያን ጽ/ቤት ከዊኪሚዲያ – ሕዝባዊ ቋት

በሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የተመሠረተበትን ምርጫ የማጭበርበር ክስ እያጥላላ ነው፡፡ ገለልተኛው ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ዋና ኃላፊ አብዲ እስማኤል ሄርሲ ምርጫው ግልጽ በሆነ መንገድ ነው የተካሄደው ብለዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ከአፍሪካ ኅብረት በመጡት ማሊያዊ ታዛቢ ሲዜ ማርያም ካይዳማ ሲዲቤ አስተያየትም የሚደገፍ ነው፡፡ እንዲህ ብለዋል፡-

የጅቡቲ ዜጎች የዜግነት ግዴታቸውን ግልፅ በሆነ መንገድ ተወጥተዋል፡፡

በፌስቡክ ገጹ[fr] የተቃዋሚው ፓርቲ አሁንም አባላቶቹ አርሂባ በተሰኘ ከተማ ለእስር እየተዳረጉ[fr]  መሆናቸውን ዘግቧል፡-

A Arhiba, la journée du dimanche 7 avril a vu l'arrestation musclée avec force brutalité d'Abdo Mohamed Ahmed et Houssein Mohamed Kamil avant d’être conduits tous deux au centre de Nagad. Puis c’est vers 2 heures du matin dans la nuit du dimanche 7 au lundi 8 avril que la police a procédé à de nouvelles arrestations directement aux domiciles des individus pour tirer de leurs lits au moins trois hommes dont les noms ont été révélés : Abdo Ibrahim Mohamed, Abdo Ali Bouha et Abbatte Gadid Merito.

እሁድ ኤፕሪል 7 በአርሂባ ከተማ፣ አብዱ መሐመድ አሕመድ እና ሑሴን መሐመድ ከሚል ወደናጋድ ከመወሰዳቸው በፊት ታፍሰው ታስረዋል፡፡ ቀጥሎም ሰኞ ኤፕሪል 8 ከለሊቱ 8 ሰዓት ፖሊስ ግለሰቦች ቤት በመግባት ከአልጋቸው በመቀስቀስ ሦስት ሰዎችን ለእስር ዳርጓል፡፡ ስማቸው የታወቁት፤ አብዱ ኢብራሂም መሐመድ እና አብዱ አሊ ቡሃ እና አባቴ ጋዲድ ሜሪቶ ናቸው፡፡

የባሕር ላይ ወንበዴዎች እንዲሁም እስላማዊ አሸባሪዎችን ለመከላከል በአፍሪካ ቀንድ ያላት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ጅቡቲ የቀድሞ ቀኝ ገዢዋን ፈረንሳይን ጨምሮ ለምዕራባውያኑ ዋንኛ ተመራጭ አጋር አገር ያደርጋል፡፡

President Ismaïl Omar Guelleh (right) with Donald Rumsfeld (left), 2002 via wikimédia Public Domain

ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ (ቀኝ) እና ዶናልድ ራምስፊልድ (ግራ)፣ 2002 – ከዊኪሚዲያ ሕዝባዊ ቋት

የቲንክ አፍሪካ ፕሬሱ ሉቃስ ሌተጎ ለምዕራቢያዊያኑ የጅቡቲን ምርጫ ለመተቸት የአገሪቱ የኋላ ታሪክ እንዴት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደከተታቸው ሲያብራራ፡-

ጅቡቲ ምናልባት ጥቂቶች የሚያውቋት አገር ልትሆን ትችላለች፣ የምዕራቢያውያኑ የውጪ ፖሊሲ አውጪዎች ግን  ከአገሪቷ እውቅናና የቆዳ ስፋት የተጋነነ ትኩረት በአፍሪካ ቀንድ የአክራሪ የእስልምና ጦር የሆነውን አልሻባብን እና የባሕር ላይ ወንበዴዎችን ለመዋጋ ዋንኛ ትኩረታቸው ናት፡፡ ምናልባትም  በሚያግባባ መልኩ ጅቡቲ የራሷን የውስጥ ችግር ከመፍታቷ ይልቅ የምዕራቡ ዓለም ጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ እና የአካባቢው ወታደራዊ ማዕከልነትና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም  ማስጠበቂያ ብቻ ናት፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.