የመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ ኢትዮጵያውንን እያሳደደ ነው?

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የት ይሆኑ ይሆን በሚለው ላይ ወራት የዘለቀው ግምት አቧርቶ በ57 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ በመደበኛ መንገድ ከተገለጸ  ወዲህ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ቢሆንም የመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ዋና ዋና ከተሞች እና የገጠር መንደሮች አውራ ጎዳናዎች ላይ በተሰቀሉ ምስሎቻቸው ኢትዮጵያውያንን አጥብቀው የያዙበት እጃቸው የመላላት አዝማሚያ አላሳየም፡፡

የመለስ ውርስ በዓለም መገናኛ ብዙኃን በመወራት ላይ ባለበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን የመለስ ውርስ የሚባለው ጉዳይ ላይ የራሳቸውን ሐሳብ ሊያንፀባርቁ በፌስቡክ እና ትዊተር ላይ ብቅ ብለዋል፡፡

ክሩቤል ተሾመ የመለስን አስቀያሚ ውርስ ሲያወሳ ለምን ብዙ ኢትዮጵያውያን የመለስን ውርስ መሬት ላይ አውርደው ለመወያየት እንደከበዳቸው በአግራሞት ጠይቋል፡፡

Portrait of the late Meles Zenawi at Meskel Square in Addis Ababa, Ethiopia. Photo courtesy of Endalk, used with permission.

የመለስ ዜናዊ ፎቶ በመስቀል አደባባይ፤ ፎቶ በእንዳልክ

ኪሩቤል እንደሚለው:-

ገነት ዘውዴ የትምህርት ሚኒስቴር በነበሩ ጊዜ እርሳቸውን አምርረው እየጠሉ መለስ ዜናዊን የሚወዱ ሰዎች ይገርሙኝ ነበር፤ በረከት ስምኦንን እየጠሉ መለስን የሚያደንቁ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እየተጠየፉ ለመለስ መልካም አንደበት የሚኖራቸው፤ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽንን እየወቀሱ መለስን የሚያፈቅሩ፡፡ አሁን መለስ ሞተዋል፣ እናም ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የነገሮች ሁሉ አድራጊ እና ፈጣሪ እንደሆኑ ተነግሮናል፡፡  ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቢያንስ ይህንን ሁሉ የትውልድ ጥፋት ላስከተለው ሰው የሚሆን የጥፋት ውርስ ለመውቀስ የሚበቃ ጨዋነት አይኖራቸውም?  ሙገሳውን ሁሉ እርሳቸው መውሰድ ካለባቸው፣ ወቀሳውንም ሁሉ እራሳቸው መውሰድ የለባቸውም?

በሌላም እንዲሁ በሚያስቆጨው የመለስ ውርስ ላይ ዐብይ የሚከተለውን ጻፈ:-

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በቀለ ገርባን፣ ኦልባና ሌሊሳን እና ሌሎችንም የሽብርተኛ ተግባር በመፈፀም ጥፋተኛ ናችሁ አላቸው፡፡ አለችን የምንላት አገራችን ይህች ናት፤ ያለችን አገር ይቺው ናት! በርግጠኝነት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞት በኋላ መለስን በማሞገስ የሚያቀነቅኑት ሰዎች የታሰሩት ሰዎች እነማን እንደሆኑም ከነጭራሹ አያውቁም፡፡

ምንም እንኳን መለስ ዜናዊ ባለራዕይ ናቸው ቢባሉም እና ውርሳቸውም መቀጠል አለበት እየተባለ ቢሆንም፤ በፌስቡክ ጽሑፉ ጆሲ ራማናት ስለመለስ ውርስ ከጓደኛው ጋር የተነጋገረውን ይዘረዝራል:-

የእሁድ ዕለት የኔና የጓደኛዬ ውይይት

ጓደኛዬ:- መለስ ዜናዊ ታላቅ መሪ የነበሩ ይመስልሃል?
እኔ:- አዎ እርግጥ ነው! ታላቅ መሪ ብቻ ሳይሆን ምናልባት ኢትዮጵያ ያየችው ምርጡ መሪያችንም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት አንተ ብዙ ጊዜ እንደምታምነው የማይተኩ ናቸው ማለት አይደለም፡፡.

ጓደኛዬ:- መለስ ታላቅ መሪ ናቸው ብለህ ካመንክ ብዙ ተቋማት በእርሳቸው ስም መሰየማቸውን ትደግፋለህ? ለምሳሌ “የሕዳሴው ግድብ” “የመለስ ዜናዊ ግድብ” ቢባል እና ምስላቸው በመቶ ብር ኖት ላይ ቢሰፍር?

እኔ: – ነገሮችን በታላቅ መሪ ስም መሰየም ምንም ችግር የለውም፡፡ ለምሳሌ፣ መቐለ ዩንቨርስቲ የኲሓ ካምፓሱን ‹‹የመለስ ዜናዊ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት›› ጅጅጋ ዩንቨርስቲም ውስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ሰምቻለሁ፡፡ እናም፣ ብዙ ዩንቨርስቲዎቸ፣ ቢሮዎች፣ ከተሞችና መንደሮች ያላቸውን ነገር ሁሉ በመለስ እየተሰየሙ ነው፡፡ “ፉክክሩን” ማን ያሸንፋል እየተባባሉ ይመስላል እና ጉዳዩ ከዚህም በላይ ገደብ ሊያጣ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፣ ትላንትና እንደሰማሁት ከትግራይ ጥንታዊ ትምህርት ቤቶች አንዱ (በነገራችን ላይ በቀድሞ ጀግናችን ስም የተሰየመ ነበር) አሁን ‹‹መለስ ዜናዊ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት›› ተብሏል፡፡ ይህ እውነት ከሆነ፣ በጣም አስቂኝ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የሚያዋርድ ነው የሚሆነው፡፡ በዛ ላይ፣ በአካባቢ ደረጃ ሊከበሩ የሚገባቸው የአንድ አካባቢ ጀግኖች አይኖሩንም ማለት ነው? ያለፉትን እንዳሉ በመተው ለአዲሶቹ አዲስ ነገር መስጠት አይቻልም? የሕዳሴውን ግድብ በተመለከተ፣ በመለስ ስም መሰየሙ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም ግድቡ ከአስጎምጂ ዕቅዳቸው አንዱ በመሆኑና ለአፈፃፀሙም ቁርጠኝነት እና ሙሉ ኢነርጂ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን ይህም ራሱ ከመለስ እምነት ውጪ ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ… ምክንያቱም እርሳቸው ‹‹የሕዳሴው ግድብ›› ብለው ሲሰይሙት በቂ ምክንያት ይኖራቸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ነገር ግን አሁንም ‹‹መለስ ዜናዊ ግድብ›› ቢባል የሚለውን ሐሳብ እደግፈዋለሁ፡፡ ነገር ግን የመለስን ፎቶ በየብሩ ላይ ማተም የሚባለው ጥሩ ሐሳብ አይመስለኝም፡፡

የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ በመለስ ዜናዊ ራዕይ የኢትዮጵያ ሕዝብን አንድ ለማድረግ በስማቸው እና በምስላቸው መጠቀሙን መቀጠል አለበት፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ የፓርቲ ሰዎች መለስን አላግባብ ፓርቲው እየተጠቀመባቸው እንደሆነ እየተሰማቸው ቢሆንም፡፡

በግልጽ ማስታወሻው፣ ክሩቤል ተሾመ የሟች መለስ ዜናዊ ባለቤት ስለባለቤታቸው እያወሩ ያሉትን ርካሽ የፍቅር ወሬ እንዲያቆሙ ጠይቋል:-

ግልጽ ማስታወሻ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን፡- እባክዎ፣ እባክዎ፣ እባክዎ ለአዲስ አበባ አስተዳዳሪዎች እርስዎ መለስ የግል ዝና እና ሰብእና ግንባታ አይወዱም በማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ የተናገሩትን የመለስ ምኞት መጣስ እንዲያቆሙ ይንገሯቸው፡፡ ምስላቸው የከተማዋ የግድግዳ ሽፋን ሆኖ ማየት እንዴት እንደሚጠሉ ነግረውናል፡፡ እርግጠኛ ነኝ አሁን፣ የከተማዋ አስተዳደር ያለምንም እረፍት ከተማዋን በመለስ ምስል ከመለስ ውርስ በተቃራኒ እያጥለቀለቀው መሆኑን አስተውለዋል፡፡ ቢያንስ ከሞታቸው በኋላ እንኳን እረፍት እንዲያደርጉ ለምን እንዳልፈቀዱላቸው ግራ ገብቶኛል፡፡ አሁንም የፀዳችና አረንጓዴ አዲስ አበባን ማየት ውርሳቸው ነበር፡፡ ስለዚህ እባክዎ ባስቸኳይ ምስሎቻቸው ከከተማዋ ግድግዳዎች፣ አጥሮች እና ሕንፃዎች ላይ እንዲነሱ ያድርጉ፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝቦች መቼም የማይዘነጉት ውለታ ይሆንልዎታል!

ሞታቸው ከተሰማ ጀምሮ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ላስመዘገበው የዕድገት ክብረወሰን ሲሞገሱ ከርመዋል፡፡ በተመሳሳይም፣ የፖለቲካ አራማጆች እና ጋዜጠኞችንም አሻሚ ትርጉም ባለው የአሸባሪነት ወንጀል በማሰራቸውም ይወቀሳሉ፡፡

1 አስተያየት

  • nega mulu

    ቤ.አድርጋው ከሆነ ይቅርታ ትጠይቅ ምክንያቱም አንዴተሳስታ ከሆነ መመለስ አይቻልም ነገር ግን ስተቱን ዓለመድገምና ከስተቱ መማር ይቻላል ድርጊቱ ጥሩነው እያልኩኝ አይደለም ሁሉም ይሳሳታልና ከስተት መማር ግን የተቀደሰ ነው እንደዚህ ምናሳዳት ከሆነ ጥሩ አይደለም አናግልላት ሁላቺንም እንሳሳታለና የነበረቺበት ሁኔታ ይከብዳል ስሜት አደገኛመሆኑን እናስታዉስ ትሳሳትይሆናልና ማግለል መጥፎመናገር ድርጊቱ እናስፋፋለንእንጅ አንቀንሰውም እኔ እንጃ ቤ.በጣም አሳዘነቺኝ

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.