ኢራን፤ እንደወንድ እየሆንክ፣ እንደሴት ልበስ

ቀይ ቀሚስ ሻርፕ እና ዓይነ እርግብ ያደረገ አንድ ሰው በማሪቫን ከተማ መንገዶች ኩርዲስታን ግዛት ኢራን ውስጥ በፀጥታ አካላት እየታጀበ እንዲጓዝ ተደረገ፡፡ በቤት ውስጥ ፀብ ምክንያት ጥፋተኛ የተባሉ ሦስት ሰዎች በከተማው መሐል የሴት ቀሚስ አድርገው እንዲጓዙ የግዛቲቱ ፍርድ ቤት ፈርዶባቸዋል፡፡ የቅጣቱ ዓይነት ለብዙዎች ግልጽ ባይሆንም በርካቶች ግን በቅጣቱ እንዲቆጡ አነሳስቷል፡፡

ማክስኞ ዕለት የዓይነ እርግብ ያደረጉ ሴቶች በማርቫን ከተማ ቅጣቱ ቀጪውን ከማስተማር ይልቅ ሴቶችን የሚያዋርድ ነው ሲሉ ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ እንደ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች የፀጥታ አካላት ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል፡፡

Men in Dress source: https://www.facebook.com/KurdMenForEquality

Shared on the Facebook page ‘Kurd Men For Equality’

በፌስቡክ በተደረገ የተቃውሞ ዘመቻ ኩርድያዊ ወንዶች ቀሚስ ለብሰው ራሳቸውን ፎቶ በማንሳት በፌስቡክ ገጾቻቸው ለጥፈዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፡-

‘ሴት መሆን ለቅጣት መሳሪያ መሆንና እና ለማዋረጃ ማስተማሪያ አይደለም’ ከላይ የሚታየው ፎቶ የኩርድ ወንዶች ለዕኩልነት የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡

ናሞ ኩርዲስታኒ እንዲህ ጽፏል፡-

ይህ ለሴትነት ያለኝን አጋርነት የማሳይበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ሴቶች በታሪክ በርካታ ችግሮች እና እንግልቶች በወንዶች አማካኝነት እንዲጋፈጡ ሆነዋል፡፡ በቅርቡ እንደተጋፈጥነው እውነታ ደደብ ዳኛ የሴቶችን ልብስ መልበስ እንደ ቅጣት  አድርጎ ውሳኔ ሰጥቷል፤ ስለዚህ ይህ ወቅት ሁላችንም በአንድነት በመቆም ይህንን የደደቦች ኢሰብኣዊና ግማሽ የኅብረተሰብ አካላትና በመሬት ላይ የሚኖሩ ግማሽ ድርሻ ያላቸውን ሴቶች የሚያንቋሽሽ ተግባር የመቃወሚያ ወቅት ነው፡፡ እኔ ማድረግ በምችለው ትንሹን ሴትነትን በመደገፍ እፈጽማለሁ፡፡

የማሪቫን ሴቶች ማህበር በበኩሉ በፌስቡክ ገፁ ድርጊቱን አውግዞ ጽፏል[fa]፡-

የፀጥታ አካላት የማሪቫን ከተማ ፍርደኛ ግለሰብን ክብር አዋርደዋል፡፡ እንደሴት አልብሰው በድርጊቱ ክብሩን እንዲያጣ ተመኝተዋል፡፡ የማሪቫን ሴቶች ማኅበር ይህንን ድርጊት ይቃወማል፡፡ እንዲሁም ድርጊቱ ሴቶችን የሚዘልፍ ነው፡፡ የኩርድሽ ሴቶች [ድርጊቱ ከተፈጸመ አንድ ቀን በኋላ] ተቃውመውታል፡፡

ኢራናዊው ጠበቃ እና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች መሐመድ ሙስጠፋ እንዲህ ብሏል[fa]፡-

የኢራን ሕግ አስፈፃሚ ይህንን የሰው ክብር የሚያዋርድ ድርጊት እንዲፈፅም የሚያስችል የሕግ ከለላ የለውም፡፡ እንደሴት መልበስን ቅጣት የሚያደርግ የኢስላሚክ ሪፖብሊክ ሕግ የለም፡

ታሪክ ራሱን ደገመ

ከሦስት ዓመታት በፊት የኢራን ባለሥልጣናት በተማሪ አራማጆች ላይ ተመሳሳይ የማዋረድ ሥራ ሊሠሩ ሞክረው ነበር፤ አልተሳካላቸውም እንጂ፡፡

ያን ጊዜ የኢራን ባለሥልጣናት የጠየቁት ማጅድ ሳቫሊን ቴህራን ላይ ንግግር ካደረገ በኋላ በተማሪዎች ቀን እንደሴት እንዲለብስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በኢራን የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች የዓይን ምስክር ጠቅሰው ሪፖርት አወጡ፡፡

‹‹በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚወጡ ማንኛውም ፎቶግራፎች ውሸት እና በተማሪዎች እና በኢራን የሚሠሩ በማኅበረሰብ አራማጆች ላይ የሚወጡ የተዛቡ የሞራል እሴት የሌላቸው ናቸው›› ብሏል፡፡ በጊዜው በመቶ የሚቆጠሩ ኢራናውያን  ወንዶች ቀሚስ ለብሰው ራሳቸውን ፎቶግራፍ በማንሳት ታቫኮሊን በመደገፍ ከጎኑ ቆመዋል፡፡

 

1 አስተያየት

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.