በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ

በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣ ብጉር ማውጣት ፀጉር ማብቀል፣ የደም ግፊት እና እንደ የሰኳር በሽታ አይነት ጉዳቶች በተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ናቸው፡፡

በሴኔጋል ቆዳን የሚያቀላው እና ‹‹ኬስ ፔች›› የተባለው ምርት የድህረ ገፅ እሰጥ አገባ ቀስቅሷል፡፡

ኬን ፋቲም ዲዎፕ ነጭ ቆዳ በ15 ቀናት በማለት ሲገልፅ፡

ሙሉ ለሙሉ ነጭ ቆዳ ማለት አንድ የምእራብ አፍሪካ ሰው ኬስ ፔችን  የሚተረጉምበት አግባብ ነው፡፡ እርሱም ቆዳን ነጭ እንደሚያደርግ ተነገረለት የክሬም አይነት ነው፡፡

አማዱ ባካሃው  DIAW Ndarinfo በተባለ ድረ ገፅ ላይ የኬስ ፔች ዘመቻ ለማንነታችን ሰድብ ባለው ፅሁፉ፡

ከ20 ቀናት በፊት ‹‹ኬስ ፔች›› የተባለ አዲስ ምርት በዳካር ዋነኛ ቦታዎች ላይ ከ100 በላይ በሆኑና እያንዳንዳቸው 12 ስኩዌር ሜትር መጠን ባላቸው የማስታወቂያ ቦታዎች ላይ ተሰቅሏል፡፡

ብሏል፡፡

ካሮል ኦድራጎ በበኩሏ NextAfrique በተባለው ድረ ገጽ ላይ ንፁህ ቆዳ በማንኛውም ዋጋ፡ በአፍሪካ ያለውን ክስተት መረዳት ባለችው ጦማሯ ድርጊቱ በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ተለመደ ተግባር እንደሆነ ስትገልፅ፡

ምርምሮች በግርድፉ ሲያስቀምጡ በማሊ፣ ባማኮ ከሚኖሩት ሴቶች ውስጥ 25 በመቶው ቆዳን የሚያቀሉ ምርቶችን ይጠቀማሉ… በደቡብ አፍሪካ ደግሞ 35 በመቶ… በሴኔጋል 52 በመቶዎቹ ሴቶች፡፡

አስከትላም፡

ሴኔጋላዊያን ሴቶች ቀላ ያለ ቆዳን እንደ ቁንጅና፣ ውበት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ግምት እንደማግኛ አድርገው ያስቀምጡታል፡፡ በታንዛኒያ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተውም ታንዛኒያዊያን አውሮፓዊ የሆነ የውበት ትርጉምን የራሳቸው አድርገው እንደያዙ ይገለፃል፡፡

ይህ በፈረንሳይኛ ቋንቋ በዩቲውብ ላይ፣ በmyskreen የተጫነ ቪዲዮ ቆዳን ለማቅላት የሚደረግ ጥረት ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ያሳያል፡፡

 

ከዳካር የሚፃፈው ኤ ቱባብ (ቱባብ ማለት በምዕራብ አፍሪካ ዘየ የምዕራቡ አለም ሰው ማለት ነው) የተባለው ጦማር The Xessalisation ማለትም ነጭ የመሆን ፍላጎት ድድብና ባለው ፅሁፉ ለምን ቆዳዎን ነጭ ያደርጉታል? ለሚለው ትያቄ ምላሽ ለመስጠት ይሞክራል፡

አንዳንዶች የሴኔጋል ወንዶች ነጣ ያለ ቆዳ ይወዳሉ፣ ስለዚህ አንዳንድ ሴቶች እነሱን ለማስደሰት ቆዳቸውን ለማንጣት ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ይህ ‹‹የበታችነት ስሜት መገለጫ›› ነው ይላሉ….

ቆዳን ማንጣት፡ በተግባር፣ ተግዳሮቱ እና ተጠያቂነት ባለው ጦማር፤ ጦማሪ ፋቱ በብላክቢዩቲባግ ጦማር ላይ ፡

ይህ ጉዳይ ከባርነት እና ቅኛ አገዛዝ ጋር ግንኙነት ያለው ነው፡፡ ከስነ ልቦና አንፃር ያለፈው ታሪክ በብዙ ሰዎች ላይ የራሱን አሻራ አሳርፎ አልፏል፡፡ ከእድል ጋር በተያያዘም የበታችነት ስሜት ሙሉ ለሙሉ አልተወገደም፡፡ [….] አንዳንድ ሴቶች በራሳቸው የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም፤ ነገር ግን ከቤተሰብ በሚመጣ ተፅእኖ እነሱም የድርጊቱ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ተፅእኖውም እንደ ጨለማ ጥቁር ነሽ፣ በጣም ከጠቆርሽ ማንም ወንድ አይፈልግሽም እና የመሳሰሉት የቃላት ግፊቶች ናቸው፡፡…

 

በዝቅተኝነት ስሜት ላይ ጦማሪ ማማ ሳራቴ ከጥቁር ወደ ነጭ ፡ በዘር ከፍ ማለት በሚል ርዕስ ክርክር ለማስነሳት አንድ ጦማር አስፍሯል፡፡

ጦማሪዎች ይሄን ጉዳይ በማንሳት እና ልማዱን ለመግታት ምን ማድረግ ይችላሉ? በታሪክ በሴኔጋል ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የቆዳቸውን ተፈጥሮአዊ ቀለም እንዳይቀይሩ የሚከክል ህግ ወጥቷል፡፡ በጃማይካ ደግሞ ጉዳዩ የህረተሰብ ጤና ጉዳይ እስከመሆንም ደርሷል፡፡ በአሜሪካ ባለፈው አመት ለእይታ የበቃው እና ዳርክ ገርልስ የተባለው ዘጋቢ ፊልም ቆዳቸው ጠቆር ያሉ ሴቶችን ህይወት እና የሚደርስባቸውን መገለል አሳይቷል፡፡  በኬንያ ደግሞ ታዋቂዋ ሞዴል አጁማ ናስናያና የቆዳ ማቅያ ምርቶችን የሚቃወም ዘመቻ ጀምራለች፡፡

 

ከቀዳሚዎቹ የጦማሪያን ተቃውሞዋች አንዱ የሆነው በኬን ፋተም ዲወፕ የተገለፀው ሲሆን፡

በተፋጠነ ሁኔታ የንቁ ዜጎች ፕሮጀክት የክሬሙን [ኬስ ፔች] ጉዳት በማህበራዊ ድረ ገፆች አጋልጧል፡፡ በሴፕቴምበር 8 የተጀመረው የድረ ገፅ አቤቱታ ዘመቻ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ማስታወቂያውን እንዲያስቆም በ4 ቀናት ውስጥ 1000 ፊርማዎችን አሰባስቦ አቤት ብሏል፡፡

@K_Sociial በትዊተር ገፁ፡

@K_Sociial: በቅርቡ ኒወል ኮክ (ሁሉም ጥቁር) የተባለ ክሬም እፈጥራለሁ፡፡ ሴቶቹም ሰማያዊ ይሆናሉ::

ያለ ሲሆን

ጦማሪዎች እና የግራፈክስ ባለሙያዎችም ይሄን ሀሳብ በመውሰድ ተቃራኒ ዘመቻ ከፍተዋል ‹‹የናንተን ኬስ ፔች (ሙሉ ለሙሉ ነጭ) ዘመቻ አይተነዋል፣ እናም ተቃራኒ የሆነውን ኒዎል ኮክ (ሙሉ ለሙሉ እንደ ዎልፍ ጥቁር) ዘመቻን ከፍተናል፡››

 

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.