ታሪኮች ስለ ቭዲዮ

ኢትዮጵያውያን #SomeoneTellSaudiArabia በሚል ስደተኞች ላይ የደረሰውን እርምጃ ተቃወሙ

ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡

ቪዲዮ፤ “ኖ ዉማን፣ ኖ ድራይቭ” ሳኡዲ አረቢያን አደመቃት

ዛሬ፣ ጥቅምት 16፣ 2006 ለሳኡዲ አራማጆች በኪንግደሙ ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የተጣለባቸው ማዕቀብ ላይ ለማመጽ የመረጡት ቀን ነበር። የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች በአገሪቷ ውስጥ መኪና እየነዱ ስለታዩት ሴቶች ቁጥር መጨመር በስፋት እያወሩ ሳሉ፣ ተወዳጁ፣ የቦብ ማርሌይ “ኖ ዉማን፣ ኖ ክራይ” የተሰኘ ዜማ ሴቶችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን ለመንፈግ የወጣ የወግ አጥባቂ ስርዓተ ፆታ...

ኢራን፤ እንደወንድ እየሆንክ፣ እንደሴት ልበስ

ቀይ ቀሚስ ሻርፕ እና ዓይነ እርግብ ያደረገ አንድ ሰው በማሪቫን ከተማ መንገዶች ኩርዲስታን ግዛት ኢራን ውስጥ በፀጥታ አካላት እየታጀበ እንዲጓዝ ተደረገ፡፡ በቤት ውስጥ ፀብ ምክንያት ጥፋተኛ የተባሉ ሦስት ሰዎች በከተማው መሐል የሴት ቀሚስ አድርገው እንዲጓዙ የግዛቲቱ ፍርድ ቤት ፈርዶባቸዋል፡፡ የቅጣቱ ዓይነት ለብዙዎች ግልጽ ባይሆንም በርካቶች ግን በቅጣቱ እንዲቆጡ አነሳስቷል፡፡

ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር

  11 ሚያዝያ 2013

ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡

“V for Vendetta” የተሰኘው ፊልም ሳንሱር አለመደረግ ቻይናውያንን አስደመመ

  22 ታሕሳስ 2012

V for Vendetta የተሰኘው እና እ.ኤ.አ. በ2005 የተሠራው፣ ስለተበደሉ ማኅበረሰቦች የሚያወራ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ቀድሞ በቻይና እንዳይ ታግዶ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ባለፈው አርብ ታኅሳስ 5/2005 በቻይና የማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (CCTV) ስድስተኛው ጣቢያ ታይቷል፡፡ በተለይም የመንግሥታትን ጭቆና ለመቃወም በመላው ዓለም ጭቆናን የመቋቋም ትዕምርት ሆኖ በአራማጆች የተመረጠው ‘V’ ሳይቆረጥ/ሳይወጣ መታየቱ በርካቶችን አስደምሟል፡፡.

በኪዌት ህቡዕ የትዊተር ገጽ ታላቅ ተቃውሞን እየመራ ነው

ባለፉት ጥቂት አመታት አመጸኞቹ በተቃዋሚ የፓርላማ አባላት በመመራታቸው ትችት ደርሶባቸዋል፤ በኋላ ወጣቶቹ የተቃውሞው መሪዎች ለመሆን ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ "የክብር ሰልፎች" ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡ሌላው አስገራሚ የሚያደርገው ነገር ደግሞ የሁለቱም ሰልፎች ቀንና መነሻ ቦታ የተወሰነው በህቡዕ የትዊተር ገጽ መሆኑ ነው፡፡

ቻይና፤ የሳንሱር ማሽኗ ለፀረ-ጃፓን እንቅስቃሴ ሲባል ቆመ?

  18 መስከረም 2012

በቻይና እና በጃፓን መካከል የዲያኦዩ (ወይም በሌላ ስሙ ሰንካኩ) ደሴት ባለቤትነት ይገባኛል ሲያይል፣ በቻይና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከ80 በላይ በሚሆኑ ከተሞች መጠነ ሰፊ ፀረ-ጃፓን ሰልፎች ተካሂደዋልል፡፡ አንዳንዶቹ ሰልፎች ወደብጥብጥ ተሸጋግረዋል፤ ነውጠኞቹ በጃፓን ስታይል የተሰሩ ምግብ ቤቶችን፣ የመገበያያ አዳራሾችን እና ሱቆችን አጥቅተዋል፣ እንዲያውም አንዳንዶቹ የጃፓን መኪናዎችን ለማቃጠል ሞክረዋል፡፡ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎች የቅርብ ክትትል በሚደረግበት እና የመንግስት ደህንነት ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ በሚተገበርበት አገር፣ ብዙዎች ይህን ያህል አመጽ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ተገርመዋል፡፡

ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ

  10 መስከረም 2012

የቻይና ትኩረት በአፍሪካ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የጨመረው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲሆን አሁን አገሪቱን የአፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ አድርጓታል፡፡ “በቻይና እና አፍሪካ መካከል የተደረገው የንግድ ልውውጥ ባለፉት 5 የ2012 ወሮች ውስጥ የዓመት ለዓመት ንፅፅሩ በ22 በመቶ ሲያድግ መጠኑ 80.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ” በማለት የቻይና የንግድ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ማይክ ኪንግ ጽፏል፡፡