ታሪኮች ስለ ዕድገት

እ.ኤ.አ.2012፤ የፍራንኮፎኖች አብዮት እና ማኅበራዊ ለውጥ ዓመት፡- ክፍል 1

  12 ጥር 2013

2012 አልቋል፤ እናም ለፍራንኮፎን (የፈረንሳይ ቅኝ [የነበሩ]) አገራት የተረጋጋ 2013 በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡ በ2012 በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ኮንጎ) እና በሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የትጥቅ ትግል ተካሂዷል፡፡ በሴኔጋል፣ ኩዊቤክ እና ፈረንሳይ ደግሞ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ በቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቶጎ ደግሞ ለውጥን የሚጠይቁ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በርካታ ክርክሮች ስደትን፣ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውሶችን እና እኩል የጋብቻ መብቶችን በተመለከተ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሆኑት ዓበይት ለውጦችን ለማምጣት ሲሆን መረጃ በመለዋወጥ ዘዴ ነው፡፡

በሴኔጋል ቆዳን ‹‹ሙሉ በሙሉ ነጭ›› የሚያደርገው ክሬም ቁጣ ቀሰቀሰ

  10 ጥቅምት 2012

በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ቆዳን ማቅላት የተለመደ እና በህግም የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ቆዳን ለማቅላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፊት ላይ ምልክት መተው፣ ብጉር ማውጣት ፀጉር ማብቀል፣ የደም ግፊት እና እንደ የሰኳር በሽታ አይነት ጉዳቶች በተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ናቸው፡፡ በሴኔጋል ቆዳን የሚያቀላው...

ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ

  10 መስከረም 2012

የቻይና ትኩረት በአፍሪካ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የጨመረው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲሆን አሁን አገሪቱን የአፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ አድርጓታል፡፡ “በቻይና እና አፍሪካ መካከል የተደረገው የንግድ ልውውጥ ባለፉት 5 የ2012 ወሮች ውስጥ የዓመት ለዓመት ንፅፅሩ በ22 በመቶ ሲያድግ መጠኑ 80.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ” በማለት የቻይና የንግድ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ማይክ ኪንግ ጽፏል፡፡