ታሪኮች ስለ እንግሊዝኛ
የሱዳን የዴሞክራሲ ፀደይ ማለቂያ ወደሌለው አስቀያሚ የበጋ ንዳድ እየተቀየረ ነው
"ትልቁ ፍራቻ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በዝምታ እየተመለከተው ሳለ፣ ዳርፉር የተከሰተው ዓይነት ደም አፋሳሽ ወታደራዊ እርምጃ እንዳይወሰድ ነው። የዳርፉርን ጭፍጨፋ የፈፀሙ ሰዎች አሁንም ኀላፊነት ይዘዋል፤ እኛ ደግሞ ከአሁኑ ፊታችንን ከሱዳን አዙረናል።"
ሊባኖሳዊው ጋዜጠኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ፌስቡክ ላይ “ስለዘለፈ” በሌለበት የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል
ፋኢድ ኢታኒ ከተሰደደበት ሃገር- ከብሪታኒያ እንደገለፀው፣ እርሱ ላይ የተላለፈው ፍርድ፣ ሊባኖስ ውስጥ የንግግር ነፃነት ወደመጨረሻው ጊዜ እየተንደረደረ ነው፡፡
የቭየትናም አዲሱ የመረጃ መረብ ደህንነት ህግ የንግግር ነፃነትን የሚደፈጥጥና የንግድ እንቅስቃሴን የሚያውክ ነው
"እንደመንግስት ማብራሪያ ከሆነ፣ ጥብቅ ቁጥጥር የአዲሱ ህግ ዋና ሃሳብ ነው፡፡"
በትልቁ የኢትዮጵያ ሐይቅ ላይ አደጋ ይዞ የመጣው አረም
የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍጥነት በማደጉ በዚያው ልክ ፍላጎቱ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ሐይቁ ላይ ያጠላበት አደጋ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ያንዣበበው ችግር ልዩ ማሳያ ትዕምርት ሆኗል።
የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ፈጣን ተቀባይነት አገኘ
የኢትዮጵያው ቦብ ማርሌይ የሚባለው ቴዲ አፍሮ፣ ምንም እንኳ ዘፈኖቹ የተሸነፈ ርዕዮተ ዓለም ይወክላሉ ቢባሉም። አልበሙ ግን የሽያጭ ሪከርድ እየሰበረ ነው።
ለምን አንዳንድ ቻይኖች በኪያኦቢ የማጠቢያ ኬሚካል ማስታወቂያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት አልታያቸውም?
"ቻይኖች ከነጮች ዕኩል ሕዝቦች መሆን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ልክ እንደነጮች ሁሉ፣ ከፍ ያለ ደረጃን መጎናፀፍ የሚፈልጉት ጥቁሮች ላይ በመቆም ነው"
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡
ኢትዮጵያ ‹ታይቶ ከማይታወቀው› የኢኮኖሚ ዕድገቷ በተፃራሪ ረኀብ ተጋርጦባታል
"ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡"
ተማሪዎች የዋና ከተማዋን የመስፋፋት ዕቅድ ለምን ይቃወማሉ?
"በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት"
ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት
ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡