GlobalVoices በ

የቅርብ ጊዜ ታሪኮች

10 ግንቦት 2013

የበይነመረብ ዘመቻ በኢትዮጵያ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ እና ዴሞክራሲ

ዞን ዘጠኝ ተብሎ በሚጠራው የጦማሪዎች እና አራማጆች ኢ-መደበኛ ቡድን አስጀማሪነት በርካታ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 2/2005 ድረስ የዘለቀ የበይነመረብ ዘመቻ አድርገው ነበር (የዘመቻው ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ አለ)፡፡ ዘመቻው ለቡድኑ ሦስተኛው ሲሆን፣ ‹‹ዴሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብት ይመለስ›› የሚል መሪ ቃል ላይ ተንተርሶ መንግሥት ‹‹በቀጥታና በተዘዋዋሪ›› እያደረገው ነው የተባለውን እገዳ ነገር ግን በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተፈቀደውን ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብት›› ራሱ መንግሥት እንዲያከብረው የሚጠይቅ ዘመቻ ነበር፡፡ በዘመቻው የተለያዩ ጦማሮች የተጻፉ ሲሆን፣ በተወሰኑ ሰዓቶች ልዩነት አብዛኛው የዘመቻው ተሳታፊ የሚያጋራቸው አጫጭር ጽሑፎች ተለጥፈዋል፣ ተሳታፊዎች ለዘመቻው የተዘጋጀውን የፕሮፋይል ምስል እንዲቀይሩ ተጋብዘው እንደተጠየቁት አድርገዋል፣ የዘመቻውን ሒደት እንዲከታተሉ የዘመቻው የኹነት ገጽ ተፈጥሯል፣ ባለፉት ዓመታት ውስጥ የተከለከሉ ሰልፎች የጊዜ መሥመር ተዘጋጅቶ ታትሟል፤ በተጨማሪም በአንድ ደቂቃ ተኩል ቪዲዮ መብቱ ለዜጎች እንዲከበር ተጠይቋል፡፡ ከፌስቡክ በተጨማሪም በትዊተር ላይ #Demonstration4Every1 እና #Assembly4Every1 በሚሉ ኃይለ ቃሎች ተሳታፊዎች ሐሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

28 ሚያዝያ 2013

ቭዲዮ ጽሑፎች
ኢራን፤ እንደወንድ እየሆንክ፣ እንደሴት ልበስ

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ

ቀይ ቀሚስ ሻርፕ እና ዓይነ እርግብ ያደረገ አንድ ሰው በማሪቫን ከተማ መንገዶች ኩርዲስታን ግዛት ኢራን ውስጥ በፀጥታ አካላት እየታጀበ እንዲጓዝ ተደረገ፡፡ በቤት ውስጥ ፀብ ምክንያት ጥፋተኛ የተባሉ ሦስት ሰዎች በከተማው መሐል የሴት ቀሚስ አድርገው እንዲጓዙ የግዛቲቱ ፍርድ ቤት ፈርዶባቸዋል፡፡ የቅጣቱ ዓይነት ለብዙዎች ግልጽ ባይሆንም በርካቶች ግን በቅጣቱ እንዲቆጡ አነሳስቷል፡፡

11 ሚያዝያ 2013

ቭዲዮ ጽሑፎች ፎቶዎች ጽሑፎች
ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ

ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡

27 መጋቢት 2013

በኬኒያ ቴሌቭዥን የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የሃይማኖት ተቋማትን አስቆጣ

በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ይውል ዘንድ HIV እና ተዛማጅ በሽታዎችን ለመከላከል የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ማስቆጣቱን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ታገዷል፡፡ ማስታቂያው አንዲት ባለትዳር ሴት ባለቤቷ ከትዳር ውጪ በሚያደርጋቸው የግብረስጋ ግንኙነቶች ኮንዶም እንዲጠቀም ምክር ስትሰጠው የሚያሳይ ሲሆን ማስታወቂያው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዩኤስ ኤድ እና ዩኬ ኤድ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተዘጋጀ ነው፡፡

21 መጋቢት 2013

ስለፍቅርና የፍቅር ጨዋታ ከአንጎላ

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ

ወጣቷ ሮዚ አልቬስ አንጎላዊ ጦማሪ (cronista) ናት፡፡ መኖሪያዋን ያደረገችው በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ውስጥ ነው፡፡ “cronista” ማለት በፖርቱጋል ቋንቋ መጦመር የሚለውን ቃል ተስተካካይ ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን - ፅሁፎቹ ባብዛኛ ጊዜ በጋዜጣ የሚታተሙ ታሪኮች አንዳንዴ እውነተኛ ተሪኮች ሌላ ጊዜ ደግሞ የፈጠራ ልብ ወለዶች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ የራስ ችሎታን በአጭሩ ያሳያሉ፡፡ “Sweet Cliché" በተሰኘው ጦማሯ አልቬስ አጫጫር ታሪኮችን የምትፅፍ ሲሆን፣ በአብዛኛው ስለፍቅር እና ስለፍቅር ጥብቅ ግንኙነቶች ትፅፋለች ( Bolgspot የፅሑፎቿ እንባቢዎች እድሜቸው ለፅሑፉ የሚመጥን ስለመሆኑ ያስጠነቅቃል)፡፡ከዚህ በታች ሰሞኑን በጣም አነጋጋሪ የነበረው ፅሑፏ ቀርቧል፡፡

20 መጋቢት 2013

ፎቶዎች ጽሑፎች
የአንድ ቬንዙዌላዊ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ውስጣዊ ምልከታ

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ የሚያድጉ ድምጾች

የቬንዙዌላ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ተማሪ መሆን ምን ይመስላል? ከትምህርታዊ ተግባቦት የወጡ ሦስት ተማሪዎች በእያደጉ ያሉ ድምፆች ትዕይንተ ሥራ ላይ ዲጂታል ፎቶዎችን እንዴት ማንሳት፣ በይነመረብ ላይ መስቀል እና ማጋራት እንደሚቻል ለመማር ተሳትፈው ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት ተማሪዎች፣ በዚህ ልዩ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከቬንዙዌላ ማኅበረሰብ የተውጣጡ እና በይነባሕላዊ እና ተግባራዊ የትምህርት ዓይነቶችን እንዲለዋወጡ የሚደረገው ጥረት ማሳያ ናቸው፡፡ በመንግሥታዊው ኢንፎሴንትሮስ [es] የተሰኘ ፕሮግራም በተዘጋጀው የዩንቨርሲቲውን የሳተላይት ግንኙነት በመጠቀም ተማሪዎቹ እንቅስቃሴዎቻቸውን፣ ንብረቶቻቸውን እና አስደናቂ ውበት የተላበሰውን እና በቦሊቪያ ውስጥ 2,000 ሄክታር ላይ የተንጣለለውን ካምፓሳቸውን በበይነመበረብ አጋርተዋል፡፡

19 መጋቢት 2013

የግራዚያኒ ኀውልት ግንባታን የተቃወሙትን መንግሥት መቃወሙ የድርዜጎችን አነጋገረ

መጋቢት 8/2005 ሰማያዊ ፓርቲ ከባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመሆን የግራዚያኒን ኀውልት ግንባታ እንዲቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ለሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ጄኔራል ግራዚያኒ ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለአምስት ዓመታት ያክል በወረረችበት ጊዜ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲጨፈጨፉ ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ በተለይም የካቲት 12/1937….. የተገደሉት ሰማዕታት ኀውልት ስድስት ኪሎ በሚባለው አካባቢ ይገኛል፡፡ ሰልፈኞቹ ከዚያ ተነስተው ወደ ጣልያን ኤምባሲ ማምራት ሲጀምሩ ያልተጠበቀ ተቃውሞ ከመንግሥት አካላት ገጠማቸው፡፡ በቦታው 43 ያክል ሰልፈኞች ታፍሰው ለእስር መዳረጋቸው አነጋጋሪ ዜና ለመሆን በቅቷል፡፡

6 መጋቢት 2013

የአድዋ ድል በዓል ጦማሪዎችን አነቃቅቶ አለፈ

ውይይት ለተሻለች ዓለም

ጥቁር አፍሪቃውያን አውሮጵያውያንን ለመጀመሪያ ጊዜ በጦርነት ያሸነፉበት የአድዋ ድል 117ኛ ዓመት በዓል የካቲት 23/2005 በብሔራዊ ደረጃ ተከብሮ ውሏል፡፡ የበዓሉ አከባበር በብሔራዊ ደረጃ እዚህ ግባ በሚባል ዓይነት ሥነ ስርዓት ባይከበርም በርካታ ጦማሪዎች፣ አስተያየቶቻቸውን በመጻፍና በማኅበራዊ አውታር ገጾቻቸው ላይ በማስፈር የበዓሉን ለዛ ጠብቀው ለማለፍ ሞክረዋል፡፡

25 ጥር 2013

ፎቶዎች ጽሑፎች
የ2013ቱን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ባንዲራ ውልብልቢት እያደመቁት ነው

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ

በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከባለፈው ዓመት የ2012 የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ሻምፒዮን ጋር በኔልስፕሩት፣ ደቡብአፍሪካ ያደረገውን ከባድ ግጥሚያ በድምቀት እያከበሩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያኑ ውብ አጨዋወት እና ከረዥም ጊዜ መጥፋት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ከታየው ድንቅ የተጫዋቾች ችሎታ ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኳሱ ጎንለጎን ማዕከላዊ የውይይት አጀንዳ ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ በስታዲየሙ ጨዋታውን ለመመልከት የገቡት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ጽሑፎችን እና ባንዲራዎችን ሲያውለበልቡ ታይተዋል፡፡

12 ጥር 2013

ፎቶዎች ጽሑፎች
እ.ኤ.አ.2012፤ የፍራንኮፎኖች አብዮት እና ማኅበራዊ ለውጥ ዓመት፡- ክፍል 1

ይህን ጽሑፍ ያንብቡ

2012 አልቋል፤ እናም ለፍራንኮፎን (የፈረንሳይ ቅኝ [የነበሩ]) አገራት የተረጋጋ 2013 በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡ በ2012 በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ኮንጎ) እና በሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ የትጥቅ ትግል ተካሂዷል፡፡ በሴኔጋል፣ ኩዊቤክ እና ፈረንሳይ ደግሞ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ በቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቶጎ ደግሞ ለውጥን የሚጠይቁ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በርካታ ክርክሮች ስደትን፣ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውሶችን እና እኩል የጋብቻ መብቶችን በተመለከተ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሆኑት ዓበይት ለውጦችን ለማምጣት ሲሆን መረጃ በመለዋወጥ ዘዴ ነው፡፡